ሴቶች ቦታ በንፁህ እስልምና

ክፍል ሰባትና ስምንት

[ክፍል አንድ] [ክፍል ሁለት] [ክፍል ሦስት] [ክፍል አራትና አምስት] [ክፍል ስድስት] [ክፍል ዘጠኝ] [ክፍል አስር]

M. Rafiqul-Haqq and P. Newton

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

 

የጋብቻ ውል ጠቃሚነት (ክፍል ሰባት)

‹የጋብቻ ውል በሕግ አውጪዎቹ የታቀደው ባል ከሴት የግብረ ስጋ ግንኙነት ብልቷና ከሌላውም አካሏ ለደስታው አላማ እንዲጠቀም ነው፡፡ በጋብቻ ውሉም ባልየው ይህንን ልዩ የሆነ ጥቅም እንደዚህ እንዲያገኝ ነው› 'Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al- 'Elmeyah, 1990, vol. 4, p. 7፡፡

‹በተለያዩ የህገ ፍልስፍና ትምህርት ቤቶች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ግንዛቤ የሚለው በጋብቻው ውል ላይ የሚደረገው ስምምነት አንድ ወንድ ከሴት እንዲጠቀም ነው እንጂ በግልባጩ አይደለም፡፡ የኢማም ማሊክ ተከታዮች መግለጫ የጋብቻ ውል የሴት የግብረ ስጋ ግንኙነት ብልቷና የሌላው አካሏን ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ነው፡፡›

የኢማም ሻፊ ተከታዮች የተናገሩት፡- ‹በጣም ተቀባይነት ያለው አመለካከት የጋብቻ ውል የተገባው በሴት ላይ መሆኑ ነው፣ ማለትም ከግብረ ስጋ ግንኙነት ብልቷ በሚገኘው ጥቅም ላይ ነው›፡፡ ሌሎች ደግሞ ያሉት፡ ‹ውል የተደረገው ለሁለቱም ለወንዶችም ለሴቶችም ነው›፡፡ ስለዚህም በመጀመሪያው አመለካከት የተነሳ ሚስት ከባሏ ዘንድ የግብረ ስጋ ግንኙነትን መጠየቅ አትችልም ምክንያቱም ይህ የእሱ መብት ነውና (የእሷ አይደለም) እንዲሁም በሁለተኛው አመለካከት መሠረት ደግሞ እርሷ ከእርሱ የግብረ ስጋ ግንኙነትን ማድረግ መጠየቅ ትችላለች›፡፡ የኢማም አቡ ሐኒፋ ተከታዮች የተናገሩት፡- ‹በግብረ ስጋ ግንኙነት የመርካት መብት የወንድ ነው እንጂ የሴት አይደለም ያም ማለት ወንድ ለግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎቱ ሴትን ማስገደድ ይችላል ማለት ነው፡፡ በሌላ ጎኑ እርሷ እርሱን ግብረ ስጋ ግንኙነት ከርሷ ጋር እንዲያደርግ ልታስገድደው አትችልም ይህም ከአንድ ጊዜ በስተቀር (በሕይወቷ)፡፡ ነገር ግን እርሱ ማድረግ አለበት ይህም ከሃይማኖት አመለካከት የተነሳ ነው፣ ይህም እርሷን ከስነምግባር ጉድለትና ብክለት ለመጠበቅ ነው› 'Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al- 'Elmeyah, 1990, vol. 4, p. 9፡፡

የጥሎሽ አስፈላጊነት (ክፍል ስምንት)

‹ጥሎሽ (ማህር) ቴክኒካዊ ቃል ነው የሚያመለክተውም በጋብቻ ውል ጊዜ የሚሰጠውን ገንዘብ ነው ይህም እርሷን ለመደሰት በሚያስችል ልውውጥ ነው› 'Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al- 'Elmeyah, 1990, vol. 4, p. 8፡፡ ‹በጣም ጠቃሚው ሁኔታ እናንተ የምታሟሉት የሴትን የግብረ ስጋ አካል ለመደሰት መብት የሚሰጣችሁ አንድ ጉዳይ ነው› Sahih Bukhari, English translation by M. Muhsin Khan, Vol. VII, Hadith No. 81. See also Mishkat al-Masabih, Book II, under section dower, Hadith No. 53፡፡

የእስልምና ኢንሳይክሎፒዲያ ከዚህ በላይ ባለው ሐዲት ላይ የሰጠው አስተያየት እንደሚከተለው ነው፡ ‹በቡካሪ ልማድ መሠረት ጥሎሽ ለጋብቻ ሕጋዊነት አስፈላጊ ሁኔታ ነው ‹እያንዳንዱ ጋብቻ ያለ ጥሎሽ ዋጋ ቢስና ባዶ ነው› Encyclopaedia of Islam, under 'Mahr'፡፡

ጥሎሽን መስጠት የአንድን ሰው የግብረ ስጋ መብት ለማስጠበቅ በጣም መሰረታዊ ነገር ነው፣ ስለዚህም ‹ማንም ሰው ሁለት ጭብጥ ዱቄትን ወይንም ተምርን ለሚስቱ እንደ ጥሎሽ ቢሰጥ በግበረ ስጋ አካሏ ላይ ሕጋዊነትን ያገኛል፡› Mishkat al-Masabih, Book II, under section dower, Hadith No. 57., reported from Abu Daud also reported by Ahmad፡፡ ሐዲቱ የመዘገበው ጥንድ ጫማ Mishkat al-Masabih, Book II, under section dower, Hadith No. 58., reported by Tirmizi፡፡ እንዲሁም የብረት ቀለበት Sahih Bukhari, English translation by M. Muhsin Khan, Vol. VII, Hadith No. 80፡፡ እንደ ጥሎሽ ይሰጡ እንደነበረ ነው፡፡ ‹በጣም ጥሩ የሆነው ጥሎሽ ለመክፈል ቀላሉ ነውና› Al-Islam wa-l-Mar'ah al-Mu'aserah, Al- Bahi al-Khuli, Dar al-Qalam, Kuwait, 1984, p. 57, reported in Musnad Ahmad፡፡

በጥሎሽና በግብረ ስጋ መደሰት ያለው ግንኙነት ከጋብቻ ግንኙነትም ውጭ እንኳን ይታያል፡ ‹አንድ ሰው ካገባች ሴት ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነትን ቢያደርግ ማለትም በስህተት እርሷን ሚስቱ እንደሆነች አስቦ፣ እርሱ ለእርሷ ጥሎሽን መስጠት አለበት ይህም በማህበረሰቡ ዘንድ ካላት ክብር ጋር እኩል የሆነ ነው፡፡ ይህም ጥሎሽ ንብረት የሚሆነው የሚስቲቱ ብቻ እንጂ የባሏ አይደለም› 'Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al- 'Elmeyah, 1990, vol. 4, p. 8፡፡

የጥሎሽ የወንድ የግበረ ስጋ ግንኙነት ደስታ ዋስትና የመሆኑ ጠቀሜታ በቁርአንም ውስጥ ተመዝግቧል፤ በሚቀጥለው አረፍተ ነገር ውስጥ እንደምንመለከተው እጅግ በጣም በታወቀው ምሁር እንደሚከተለው ተገልጧል፡

(እንደዚህ ዓይነት ሚስቶች እየተደሰታችሁባቸው የሚገባቸውን ደሞዛቸውን  ስጧቸው ቁርአን 4.24)፡፡ (በዚህ ቁራናዊ ጥቅስ ላይ የተጠቀሰው ደስታ) ግብረ ስጋዊ ደስታ ነው፡፡ እንዲሁም ዋጋው (ደሞዙ) ጥሎሽ ነው፡፡ ጥሎሽ ደሞዝ ተብሏል ምክንያቱም የደስታ ደሞዝ ነውና ... ይህም የሚያረጋግጠው ደሞዙ ለሴት የግበረ ስጋ ግንኙነት ብልት ለውጥ ነውና (ወይንም ለሚደረገው የግብረ ስጋ ግንኙነት)፣ ስለዚህም ለደስታ ለውጥ የተሰጠው ነገር የሚጠራው ደሞዝ ተብሎ ነው፡፡ ምሁራኑ በጋብቻ ውል የተደረገበት ነገር ምን እንደሆነ አይስማሙም፡፡ ለሴቷ አካል (ብልት) ነውን፣ ወይንስ ከሴቷ የግብረ ስጋ ግንኙነት የተነሳ ከሚመጣው ደስታ ጋር ነውን? ወይንስ ከሁለቱም? ግልፅ የሆነው ነገር ግን ከሁለቱም ነው ምክንያቱም ውሉ የሚያሳየው (የሚጠቅሰው) እነሱን ሁሉንም ነውና› Qurtubi፡፡

የዚህ የጥሎሽ አስፈላጊነት በሐዲትም ላይ ተመስክሮለታል፡ ‹አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ድንግል ናት በማለት አግብቷል፡፡ እርሱም ካደረገችው ዝሙት እርጉዝ መሆኗን በመረዳት ለነቢዩ ሪፖርት አደረገ፡፡ ነቢዩም የወሰነው ሴትየዋ ጥሎሽ እንደሚገባት ነበር፡፡ እርሱም ሁለቱንም አለያያቸው እና ሴትየዋ እንድትገረፍ አዘዘ ከዚያም ለሴትየዋ አላት፡ ‹ልጁ ያንች ባሪያ ይሆናል (በእስልምና ሕጋዊ ያልሆነን ልጅ ጉዲፈቻ ማድረግም ሆነ እውቅና መስጠት በፍፁም አይቻልም) Encyclopaedia of Islam, under 'Nikah'፡፡ ስለዚህም ጥሎሹ የተሰጠው ለግበረ ስጋ ግንኙነቱ ለውጥ ሆኖ ነው› Ibn Kathir, commenting on the Q. 4:24፡፡

‹ጥሎሽ የተሰጠው ለሴቶች የግብረ ስጋ ግንኙነት ብልት ለውጥ ሆኖ ነው› Ibn Kathir, commenting on the Q. 4:24፡፡ ‹በምስስል ጥሎሽ መሰጠት ያለበት የሴትን የግብረ ስጋ ግንኙነት ብልት ለመጠቀም ወይንም በዚያ ለመገልገል ነው› Razi, commenting on Q. 4:25፡፡

‹(ለነርሱም በርሱ (በመገናኘት) የተጠቀማችሁባቸውን ሴቶች መህሮቻቸውን ግዴታ ሲሆን ስጧቸው) ቁርአን 4.24) ያንን ጥቅስ በተመለከተ ሁለት ትርጉሞች አሉ፡፡ የመጀመሪያው የብዙዎቹ ምሁራን አመለካከት የሆነው ‹ለናንተ ግዴታ ሲሆን  የሚለው ማለትም የናንተን ንብረት በጋብቻ ውስጥ ልትጠቀሙበት ትፈልጉ ይሆናል›፡፡ ይህም ማለት በንብረት ሴትን ለማግባት መፈለግን ነው፡፡ ሌላው ትርጉም የሚለው ጥቅሱ የሚያወራው ስለ ጊዜያዊ ጋብቻ ነው የሚል ነው›) Razi, commenting on Q. 4:24፡፡

‹አቡ ባክር አር-ራዚ እንዲህ አለ፡ ‹ይህ ጥቅስ (ቁርአን 4.24) ባሪያ ሴትን ነፃ ማውጣት የእርሷ ጥሎሽ ሊሆን እንደማይችል ማስረጃ ነው›፡፡ ምክንያቱም ይህ ጥቅስ የሚያስረዳው የሴት የግብረ ስጋ ግንኙነት ብልት የገንዘብ ዋጋ ያለው ነገር መሆኑን ነው› Razi, commenting on Q. 4:25፡፡

‹ማሊክ እንዲህ አለ፡ አንድ ጥሎሽ ከአንድ ዲናር አንድ አራተኛ ያነሰ መሆን የለበትም፣ ወይንም ሦስት ዲርሃሞች፡፡ አንዳንድ የእኛ ተከታዮች የዚህን ግኝት ትክክልነት እንደሚከተለው ገልፀውታል፡ ይህ የሚመስለው እጅን ከመቁረጥ ጋር ነው ምክንያቱም የሴት የግብረ ስጋ ግንኙነት ብልት የአካሏ ክፍል ነው እንዲሁም እጅ የአካል ክፍል ነው ይህም የሚቆረጠው ገንዘብ ከሰረቀው ሰው፤ ከአነስተኛው ስርቆት ጋር ተመጣጣኝ እንዲሆን ተደርጎ ነው፡፡ ያም የአንድ ዲናር አንድ ሩብ ወይንም ሦስት ዲርሃሞች ነው፡፡ ስለዚህም ማሊክ ያየው (የወሰደው) የሴት የግብረ ስጋ ግንኙነት አካል እንደ አንድ እጅ እኩል ዋጋ እንዳለው አድርጎ ነው፡፡ አቡ ዑማር እንዲህ አለ፡ ‹አቡ ሃኒፋ በፊቱ ወደ ተመሳሳይ መደምደሚያ መጥቷል፡፡ እሱም ጥሎሽን ከእጅ መቁረጥ ጋር አመሳስሎታልና፡፡ በሱም ዘዴ ውስጥ እጅ ስለ አንድ ዲናር ወይንም አስራ ሁለት ዲርሃሞች እኩል ካልሆነ በስተቀር ሊቆረጥ አይቻልም ስለዚህም በእሱ መሠረት ከዚህ በታች ያነሰ ጥሎሽ አይሰጥም› Qurtubi, commenting on Q. 4:24፡፡

‹አላህ እያለ ያለው (ሀብታችሁን በጋብቻ ውስጥ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ) ማለትም፡ በጋብቻ ውስጥ ወይንም በግዢ ነው፡፡ ስለዚህም አላህ፤ ጥበበኛው፤ የሴትን የግብረ ስጋ ግንኙነት ብልት በሐብት ሕጋዊ አድርጎታል፡፡ ያም ደግሞ በጋብቻ ውስጥ ጥሎሽን መስጠት አስፈላጊ አድርጎታል፡፡ ታላቁ አላህ የሴቶችን የግብረ ስጋ ግንኙነት ብልት ጥሎሽ ሳይከፈል (ዋጋ ሳይከፈልበት) መጠቀምን ሕገ ወጥ አድርጎታል› Abu Bakr Mohammad Ibn 'Abd Allah known as Ibn al-'Araby, Ahkam al-Qur'an, Part 1, p.387፡፡)

‹መህሮቻቸውን (ደመወዛቸውን) ግዴታ ሲሆን ስጧቸው› ቁርአን 4.24፡፡ ይህ ጥቅስ የሚያስረዳው ጥሎሽ (ደመወዝ) ተብሎ መጠራቱን ነው፡፡ የዚህም ማስረጃ የሚገኘው ጥሎሽ የሚሰጠው በግብረ ስጋ ግንኙነት ለመርካት ጥቅም ሲባል ስለሆነ ነው፡፡ ምክንያቱም ጥቅሙ ደመወዝ ተብሎ የተጠቀሰው በንፅፅር ነውና› Abu Bakr Mohammad Ibn 'Abd Allah known as Ibn al-'Araby, Ahkam al-Qur'an, Part 1, p. 401፡፡ ‹ምሁራኖቻቸን የተናገሩት፡ ‹አላህ፤ በጣም ታላቁ፤ እርሱ ጥሎሽን ምትክ አድርጎታል፡፡ እርሱም ያየው ምትክ እንደሚፈልጉት ልክ እንደሌሎቹ ነገሮች አደርጎ ነው፡፡ ምክንያቱም እርሱ እንደሚከተለው በመናገሩ ነው፡ (የተጠቀማችሁባቸውን ሴቶች መህሮቻቸውን ግዴታ ሲሆን ስጧቸው› 4.24፡፡ ስለዚህም እርሱ ደመወዝ ብሎ ጠርቶታል፡፡ እርሱም ከስጦታ ሕግ ውጪ አውጥቶት እንደ ምትክ ሕግ አድርጎ ቆጥሮታል፡፡ ስለዚህም በጋብቻ ውስጥ ሁለቱም ተጋቢዎች እርስ በእርስ መደሰት አለባቸው ጥሎሽ ደግሞ ለሚስት ተጨማሪ ክፍያ ነው የሚለው ክርክር ትክክል አይደለም፡፡ ነገር ግን ባል ጥሎሽን መስጠት ግዴታ አለበት፣ ይህም በሴት ላይ የገዢነትን መብት እንዲያገኝ፣ እንዲሁም ጌታ በባሪያው ጌታ ላይ ሆኖ እንደሚቆመው ነው ይህም በምትክነት ከሰጠው ስጦታ የተነሳ ነው፡፡ ስለዚህም የእሷ ጥቅም ሁሉ የእሱ ሆኗል፡፡ በሆኑም እርሱ ካልፈቀደ በስተቀር እርሷ ልትፆም አትችልም፡፡ እርሱ ካልፈቀደ በስተቀር ወደ ሐጂም ልትሄድ አትችልም፡፡ እርሱ ካልፈቀደ በስተቀር ቤትንም ለቅቃ ለመውጣት  አትችልም፡፡ እርሱም በእርሷ ንብረት ሁሉ ላይ መብት አለው፤ አንድ ሦስተኛው የእርሷ ከመሆኑ በስተቀር፡፡ በእርሷም አካል ላይ እርሱ ያለምንም ንግግር መብት አለው፡፡› Abu Bakr Mohammad Ibn 'Abd Allah known as Ibn al-'Araby, Ahkam al-Qur'an, Part 1, p 317፡፡

ኢብን አል አራቢ የተገነዘበው ነገር፤ ጥሎሽን በመክፈል የሚገኘው የወንድ የግብረ ስጋ ግንኙነት መብት፤ በቁርአን ውስጥ መሰረት ያለው እውነታ እንደሆነ ነው፡፡ እንዲያውም በመቀጠል የተናገረው ጥሎሽን መክፈል በባልና በሚስት መካካል የባሪያና የጌታ ዓይነት ግንኙነትን እንዳመጣ ነው፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ

ሴቶችን በተመለከተ በንፁህ እስላም ውስጥ ስላለው አመለካከት በተከታታይ ያየናቸው እውነታዎች አንባቢዎችን እንደሚያስገርሙ ምንም ጥርጥር የሌለው ነገር ነው፡፡ ከዚህ በላይ ባለው ክፍል ውስጥ ያየናቸው የጋብቻ ውል እና ጥሎሽ በሴቶች ላይ ካለው አጠቃላይ አመለካከት ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡

በእስልምና የጋብቻ ውል ጠቀሜታው በሴት የግብረ ስጋ ግንኙነት ብልት ላይ ወንድ እንደፈለገ መብትና ስልጣን እንዲኖረው፣ ጥሎሽም የሚሰጠው የሴትን የግብረ ስጋ ግንኙነት ብልት ወንዱ የራሱ መጠቀሚያ እንዲያደርገው መብትን ለመስጠት እንደሆነ ነው፡፡

በእስልምና ሴቶች የሚታዩት እንደ ፍጡርና የትዳር ጓደኞች ሳይሆን ለወንዶች የግል ስሜት ማርኪያ ተደርገው ብቻ ነው፡፡ ይህ አመለካከት የፈጣሪ ሐሳብ መሆኑ አጠራጣሪ እና አስደንጋጭም ረባሽም ነው፤ እንደ እውነቱ ከሆነ አስደንጋጭነቱ ለሴቶች ብቻ ሳይሆን ለወንዶችም ነው፡፡ በሴቶች ላይ ያለው የእስልምና አስተምህሮ፣ የጥንታዊዎቹም ሆኑ የዘመናዊዎቹ የሙስሊም ሊቃውንቶች ትርጉምና አመለካከት ተመሳሳይ መሆኑም ሌላው አስገራሚ እንዲሁም አስደንጋጭ ነገር ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስና የመጽሐፍ ቅዱሱ ክርስትና ግን ለሴቶች ያለው አመለካከት በጣም የተለየ ነው፡፡ ከመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ጀምሮ እስከ መጨረሻው እንደተጻፈው ሴቶች እንደ ወንዶች ክቡር የሆኑ ፍጡራን ናቸው፡፡ ሴቶች ከወንዶች ዝቅ ተደርገው ወንዶች ደግሞ ከሴቶች ከፍ ተደርገው የሚታዩበት ምንም ምክንያት እልተሰጠም፡፡ ሕያው የሆነው እውነተኛው ፈጣሪ በቃሉ ላይ ስለ ሴት መፈጠር የተናገረው ሴቶች ለወንዶች እረዳት እንዲሆኗቸው፣ በጋብቻ ጥምረት የተነሳም ሁለቱ አንድ አካል እንደሆኑ፣ ማንም ይህንን ጥምረት ሊለየው እንደማይችል እንደማይገባም በግልጥ ተቀምጧል፡፡ በፍጥረቱ ሕግጋትም መሠረት አንድ ወንድ ማግባት ያለበት አንዲትን ሴት ብቻ እንደሆነ አሁንም ግልጥ ነው፡፡

ወንዶች ሴቶችን እንዲያከብሯቸው፣ እንዲወዷቸው፣ ራሳቸውን እንደሚንከባከቡ እንዲንከባከቧቸው በግልፅ ታዘዋል፡፡ እነዚህን ትዕዛዛት በክርስትያን ወንዶች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው እጅግ በጣምም የሚደሰቱባቸውና አምላካቸውን በማክበር ከእምነት እህቶቻቸው ማለትም ሚስቶቻቸው ጋር በሰላምና በደስታ በእኩልነትም የሚኖሩበት ምንጭ ነው፡፡ ክርስትያን ሴቶችንም የሚያፅናና በሰዎች መካከል አድልዎ የማያደርገው የእውነተኛ አምላካቸው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው፡፡ ይህ አመለካከት በባህል በዘር በሰዎች ኃጢአታዊ እና በባህላዊ እን ልዩ የሆነ ፓጋናዊ ሃይማኖት አስተሳሰቦች አማካኝነት ተፅዕኖ ሊደረግበት አይገባም፡፡

ስለዚህም ለሙስሊም ወንዶችም ሆነ ሴቶች የምናቀርበው ጥሪ፣ ስለ እስልምና በጊዜው ከሚገለጡት እውነቶች አኳያ እምነታቸውን እንዲመረምሩ ነው፡፡ የምንከተለው እምነት እውነተኛ የመሆኑ ጉዳይ ወሳኝ ለዚህ ምድር ሕይወት ብቻ ሳይሆን ለዘላለምም ሕይወት ወሳኝ እንደሆነ ልታስቡ ይገባል፡፡ ስለዚህ ወደ መጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር እምነት እንትመጡ በፊቱም እርሱ ብቻውን ባዘጋጀው የደኅንነት መንገድ በመቅረብ ስለ ኃጢአታችሁ ንስሐ በመግባት በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል እንዲቀበላችሁ ይቅርታ እንድትጠይቁት ነው፡፡ ለዚህም እንዲረዳችሁ ይህንን ገፅ እንድትከታተሉ መጽሐፍ ቅዱስን በመፈለግ አንድታነቡ እንመክራችኋለን፡፡ ጌታም በምህረቱ አዲስን ሕይወት በመስጠት ሙሉ እረፍትና ሰላምን ያበዛላችኋል፡፡ እግዚአብሔር በምህረቱ ይረዳችሁ ዘንድ የዘወትር ፀሎታችን ነው፡፡

ወደ ክፍል ዘጠኝ ይቀጥሉ፡፡

የትርጉም ምንጭ:  The Place of Women in Pure Islam  

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ