መስጊድ እና በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለው ሚና

በባልታዛር እና አብደናጎ

ቅንብር በአዘጋጁ

በተከታታይ የምናቀርበውና The Mosque and its Role in Society በሚል ርዕስ የተጻፈው ትንሽ መጽሐፍ መቅድምና መግቢያ ጸሐፊዎቹ ስለመስጊድ በጥልቀት ያጠኑትንና በተከታታይ ስለምናቀርበው እውነታ ፍንጮችን ለመጠቆም የሚያገለግል ክፍል ነው፡፡ ስለ ሙስሊሞች መስጊድና በውስጦቻቸው ስለሚከናወኑት እንቅስቃሴዎች የምውቀው ምንያህል ነው?  ከዚህ መግቢያ ቀጥሎ በተከታታይ የሚቀርቡትን ጽሑፎች ማንበብ በሕይወታችን ውስጥ ለምንወስደው እርምጃ መሰረታዊ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

 

ማውጫ

  1. ክፍል አንድ
  2. ክፍል ሁለት
  3. ክፍል ሦስት
  4. ክፍል አራት
  5. ክፍል አምስት
  6. ክፍል ስድስት

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

መስጊድ ምንድነው? እንደ ክርስትያኖች ቤተክርስትያን፣ እንደ አይሁዶች ምኩራብ ወይንም ቤተመቅደስ፣ እንደ ሂንዱዎች ቴምፕል በመሆን ለሃይማኖት ስርዓት ብቻ የቆመ ስፍራ ነውን? ወይንስ ሌላ?

ይህንን መረዳት ለሙስሊም አንባቢዎችና ለሌሎች ምን ይጠቅማል? በመስጊድ ውስጥ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችና ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎች በተለያዩ ጊዜዎች ውስጥ ስለምን ተገኙ?

እነዚህን ጥያቄዎች የሚዳስሰውን ይህን መጽሐፍ በጥንቃቄ ማንበብ የዕውቀት አድማሳችንን ማስፋት ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር የሰጠንን ሰብዓዊ ሕሊና ሊጠይቅ የሚገባውን መሰረታዊ ጥያቄ እንዲጠይቅ ያነሳሳዋል፡፡ አንድ ሃይማኖት በማኅበረሰቡ ውስጥ ሊኖረው የሚገባው ሚና ምንድነው? የሃይማኖት ተቋማትና ማዕከላት መሆንና ማራማድ ያለባቸው ምንድነው? የሰው ልጅ ዘላለማዊና ዋናው ፍላጎቱ ምንድነው? የእነዚህን ጥያቄዎች መልሶች ልናገኛቸው የምንችለው ከየት ነው?

አንባቢዎች ሆይ ይህን “ለእስልምና መልስ” ድረ ገፅን በተከታታይ እንድታነቡ እየጋበዝን ለእነዚህ ጥያቄዎች በበኩላችሁ መልሶችን ከመፈለግ እንዳታቋርጡ እናሳስባለን፡፡ ሰዎችን ሁሉ ወደ ፍቅርና ሰላማዊ መንግስቱ የሚጋብዘው የፀጋ ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ይርዳችሁ አሜን፡፡

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ