መስጊድ እና በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለው ሚና

በባልታዛር እና አብደናጎ

መግቢያ

መስጊዶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአምልኮ ስፍራነት ባለፈ - በታዋቂው የሴፕቴምበር 9/2011 የኒው ዮርኩ የዓለም የንግድ ማዕከል ላይ ከደረሰው ጥፋት አስቀድሞ በማድሪድ የተከሰተው የባቡር ላይ ጥቃት እንዲሁም የቅርብ ጊዜው በለንደን የተደረገ የአውቶቢስ እና የውስጥ ለውስጥ ባቡሮች ላይ ጥቃትን በተመለከተ - ያደረጉት አስተዋፅዖ ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ የምዕራባውያን የዜና አውታሮች አያሌ አንቀፆችን በጉዳዩ ላይ እንዲያስነብቡ አድርጓቸዋል።

ለምሳሌ፣ ሁለቱም ዘ ታይምስ እና ዘ ጋርዲያን ጋዜጦች በፊንስበሪ መስጊድ (ዘ ታይምስ፣ ጃንዋሪ 12, 1999፤ ዘ ጋርዲያን፣ ጃንዋሪ 16, 1999) በመካከላቸው ይደረጉ ስለ ነበሩና ቀጥሎም በየመን በተደረገ የአሸባሪዎች ዘመቻ ውስጥ ሚና እንደ ተጫወቱ ስለ ተነገረላቸው ፖለቲካዊና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በቅርቡ ጽፈዋል። እነዚያ አንቀፆች ከመስጊዶቹ ጋር በተለየ ሁኔታ የተያያዙት እስላማዊ ትምህርት ቤቶች (መድረሳዎች) ግለሰቦቹን በማሠልጠን ረገድ እንዲሁም እንዲህ ያሉ ሐሳቦች እና ድርጊቶች ይስፋፉ ዘንድ እንደ ማነቃቂያ ጠቅመው እንደሆነም አጠያይቀዋል።

በምስራቅ ለንደን ጥቃት በደረሰበት ማኅበረሰብ አውራ-ጎዳናዎች ላይም እንዲሁ የ2005 የአለም የኦሎምፒክ ጨዋታ በሚጀምርበት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የታሰበውን ትልቅ መስጊድ ግንባታ በተመለከተ ተመሳሳይ ስጋቶች በዜና አውታሮች ተንፀባርቀዋል።

በዓለም ላይ ካሉት መስጊዶች ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው ሊገነባ የታሰበውን የኒውሃም መስጊድ አቅም እና የስነ-ሕንጻ ውበት ይወዳደራሉ ተብሎ የሚታሰበው። እንዲህ ያለ ግዙፍ ሕንጻ በሠላማዊው መንደር መካከል መገንባቱ ለመረዳት የማያዳግቱ አካባቢያዊ ስጋቶችን አስነስቷል። ቢሆንም፣ እንዲህ ያሉ የተለምዶ ስጋቶች (ጥቂቶቹን ለመዘርዘር፤ የመኪናዎችን እንቅስቃሴ ማስተጓጎል፣ የድምጽ ብክለት፣ የንብረቶች እሴት፣ . . . ) እንዲህ ያለው መስጊድ እንዳይገነባ ለማድረግ በቂና ፍትሐዊ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉን? እርግጥ ነው፤ የዚህ ፕሮጀክት አንቀሳቃሾች ይህንን ሁሉ አስቀድመው ያሰቡበት መሆኑ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ከመስጊዱ ግንባታ የተነሳ ያገኟቸዋል ተብለው የሚጠበቁ አካባቢያዊና ሀገራዊ ጥቅማ-ጥቅሞችን በተመለከተ ቀደም ብለው ያዘጋጇቸው ቀልብ የሚስቡ ዘገባዎች መኖራቸው አይጠረጠርም። እንዲያውም ቀደም ብለው  ባለሥልጣናቱ “ዩ. ኬ. ባስቀመጠው የእምነት ነፃነት፣ የአምልኮ እንዲሁም ራስን የመግለፅ መብት መለኪያ መሠረት” ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ተፅዕኖ ሊያደርጉባቸው እንደ ሞከሩ ይታመናል።

ስለዚህ መስጊድ ምን እንደ ሆነ፣ ተግባራቱ ምን ምን እንደሆኑ፣ በተለይም ደግሞ ማኅበረሰባዊ ግንኙነቶችን ያዳብር እንደሆነ፣ በተገነባበት ማኅበረሰብ መካከል ሰላማዊ የመቻቻል ኑሮን ያበረታታ እንደ ሆነ፣ እንዲሁም የተለያዩ ቤተ እምነቶች እንቅስቃሴያቸውን ያለ ምንም መስተጓጎል ማድረጋቸውን ይቀበል እንደ ሆነ መጠየቅና መፈተሻችን ተገቢ ነው።

ይህ ሊመዘን የሚችለው የእስልምና መሠረተ-እምነት ቀዳሚ ምንጮች የሆኑት ቁርኣን እና ሱና እንዲሁም ከእነዚህ ሁለት ምንጮች የተውጣጣው የሕግ አካል የሸሪዓ ሕግ  የሚመክሩትን እና የሚያስፋፉትን አካሄድ በማጤን ነው።

አንባቢዎች በመስጊዶች ውስጥ የሚከናወነውን ፖለቲካዊና ወታደራዊ አስተሳሰብና እንቅስቃሴ የሚደግፉ አዋጆችን በተመለከተ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚያስችሏቸው ምስሎች፣ የእስላም ዋና ዋና ጸሓፊዎች ያሰፈሯቸው ጽሑፎች እንዲሁም ፋትዋ በመባል የሚታወቁት የሕግ ድንጋጌዎች በዚህች አነስተኛ መጽሐፎች ውስጥ ተካትተዋል።

አያሌ ወቅታዊ ጉዳዮች በሸሪዓው ምክር ቤት ውስጥ ባለው ኡላማ  (ኡላማ ካላቸው ዕውቀት የተነሣ የሸሪዓ ሕግ ባለው ነባራዊ ሁኔታና ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት እንዲኖረው የመተርጎም ሥልጣን የተሰጣቸው ወንዶች ስብስብ ነው) በሚጣሩበትና ወደየመስጊዶቹ በሚመለሱበት ጊዜ፣ ከእነዚያ አዋጆች የሚነሱት እርምጃዎች ልዩ ልዩ ፖለቲካዊና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ፍተሻ ተካሂዶባቸው ወደ ትግበራ ይገባሉ። እነዚህ ድንጋጌዎች ጠፍረው የሚይዙና አንዳች ጥያቄ ለማንሳት የማይፈቅዱ ስለሆኑ በየመስጊዱ የሚገኙ ምእመናን እና መሪዎች በግላቸው ሊያስቡና ሊያመዛዝኑ የሚችሉበትን ዕድል አይሰጥም።

ነገር ግን፤ ይህ በመስጊዶች ውስጥ ተፈፃሚነት የሚኖረው የመጨረሻ ድንጋጌ (ምስል 3ን ይመልከቱ) በመጀመሪያ የሚነሳው ኡላማው ሊወስንባቸው የሚያስፈልጉ ዕቅድ የማውጣት፣ የማስተማር፣ ወ.ዘ.ተ ጉዳዮች ከሚገኙበት ከዚያው ከመስጊድ ውስጥ ነው። እነዚያ ከየአካባቢው መስጊዶች የኡላማው አባላት ወደ መሆን የሚያድጉት ሙስሊሞች በተመሳሳይ ጊዜ ፋትዋው እንዲታወጅ የሚያደርጉ የመስጊድ መሪዎች፣ ሰባኪዎች፣ ምሑራን እና ዳኛዎች ናቸው። አዋጆቹን ያጠናሉ፣ ያብራራሉ፤ እንዲፈጸም ያደርጋሉ! ከቁርኣን በተውጣጡ ሕገ ደንቦች ላይ የተመሠረቱ እንደ መሆናቸው አሠራራቸው ለጥያቄም ሆነ ለውይይት አይቀርብም።

የዚህን እንቆቅልሽ ፍቺ ለማግኘት አያሌ ሽርፍራፊዎችን ስንገጣጥም በአይሁድ እና ክርስትና ንፅረተ-ዓለም ውስጥ የተለመዱ የሚመስሉ ነገር ግን የሚታወቁ መምሰላቸው በፊደል አንድነት ብቻ የሆኑ ቃላት የሚፈጥሩትን ግርዶሽ ለመፍታት እንጥራለን። ስለዚህ የቃላት አጠቃቀማችንን እና አስቀድማችሁ እንደምታውቋቸው የምታስቧቸውን ቃላት ፍቺ ማስቀመጣችንን እንደ ስሕተት እንዳትቆጥሩት እንጠይቃችኋለን።

በእስልምና አካሄዶች እና ዶሴዎች ውስጥ ኅብረተሰባዊ እና ፍትሕ ነክ የእስላማዊ ግንኙነቶችን በተመለከተ መስጊድ ማዕከላዊው እንዲሁም መነሻና መደምደሚያው ስፍራ እንደሆነ በተሻለና በጠራ ሁኔታ ለማሳየት በአዳዲስ ቃላቶች (እንደ ተቂያ ባሉ) እንዲሁም በተለመዱ (እንደ ጀሐድ እና ሒጅራ) ያሉ ቃላት ላይ እንሠራለን።

ይህ አነስተኛ መጽሐፍ በጥንቃቄ ቢነበብ የዕውቀት ማነስ የሚያስወግድና በዘመናችን እጅግ አንገብጋቢ በሆኑ፣ ነገር ግን ቸል በተባሉ ተቋማት ላይ ያለንን ግንዛቤ የሚያዳብር ይሆናል።

ወደ ማውጫው መመለሻ

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ