መስጊድ እና በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለው ሚና

በባልታዛር እና አብደናጎ

መቅድም

ይህ መጽሐፍ፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዜና አውታሮች በተደጋጋሚ በመነገር ላይ ያለው፤ በዩናይትድ ኪንግደምና በአውሮፓ በሚገኙ ዋና ዋና መስጊዶች ውስጥ መሣሪያዎችና ሽብርተኝነትን የሚያስፋፉ ጽሑፎች ተገኝተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ መጽሐፍ በአሁኑ ጊዜ በምዕራባውያን አመለካከት ይዘቱ እንደ ቤተ ክርስቲያን ወይም ቤተ መቅደስ ሁሉ የአምልኮ ስፍራ ሆኖ የሚቆጠረውን መስጊድ ያተኮረ ጥልቀት ያለው ዘገባ ነው። የተገኙት መሣሪያዎችና ጽሑፎች - ይህ ዘገባ በዋነኛነት የሚዳስሰውን - አንድን ጠቃሚ ጥያቄ፣ እንዲያውም የጥያቄዎች ስብስብ አስነስተዋል። ጥያቄዎቹም “መስጊድ የአምልኮ ስፍራ ብቻ ነውን? ከሆነ ደግሞ፤ በውስጡ ሲካሄዱ እንደተገኙት ያሉ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች የሚደረጉበት እስላማዊ አምልኮ ምን ቢያካትት ነው? ደግሞም በዋነኛነት፤ እነዚህ ድርጊቶች እስልምናን በእርግጥም የማይወክሉ ከሆኑ ለምንድን ነው የሚመለከታቸው እስላማዊ ባለ ሥልጣናት የተቃውሞ ድምፃቸውን ያላሰሙት?” የሚሉትና እንደዚህ የመሳሰሉት ናቸው። በልዩ ልዩ ባለ ሥልጣናት የተደረጉ የይቅርታ ጥያቄዎችና ገለፃዎች ቢኖሩም ስለ ንፅህና የሚደረጉት ማስተባበያዎች እንደዚያ ያሉት ድርጊቶች በተደጋጋሚ እንዲፈጸሙ የሚያበቃ አሳማኝ ምክንያታዊነት የላቸውም። ከልባቸው ከሆነ በመስጊዶች ውስጥ የሚደረገውን እንዲህ ያለ እንቅስቃሴ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚያስቆም ፋትዋ ወይም የሕግ ውሳኔ እንዲጸድቅ አያደርጉምን?

ከላይ የተጠቀሱትና እንደነርሱ ያሉ ጥያቄዎች ናቸው ነባራዊ ሁኔታውን፣ ዳራውን እና እንዲህ ያለ ጥናት የማካሄዱን አስፈላጊነት ለደራሲዎቹ ያቀበሏቸው።

ነገር ግን፤ ይህንን ጥናት ለማካሄድ አንገብጋቢ ምክንያት የሆነው፣ ለመሠራት በዕቅድ ላይ ባለውና በ2012 የበጋ የኦሎምፒክ ጨዋታ ወቅት ተጠናቅቆ 70,000 አማንያንን ሊይዝ እንደሚችል በታለመለት በምስራቅ ለንደኑ ኒውሃም ሊገነባ ባለው ታላቅ መስጊድ እወጃ ወቅት ግልፅና ወቅታዊ አደጋ መታየቱ ነው። ነገሩ በደረሰበት ማኅበረሰብ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በግልጽ በሚታይ ሁኔታ በነገሩ የተደናገጡ ሲሆኑ ለእነዚህ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሾችን ይፈልጋሉ፤ ምላሾቹንም የሚሹት አሁን፣ ጊዜው ሳይረፍድና ምክንያታዊ ግምገማ ሊካሄድ በሚቻልበት ወቅት ነው።

የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊዎች በፈቃዳቸው እስልምናን የተዉ ሲሆን፣ እስላማዊ ባልሆኑ ሀገራት ውስጥ ያለንን የምርጫ ነፃነት የማስጠበቅን አስፈላጊነት እንዲሁም ይህ መስጊድ (ወይም ሌላ የትኛውም መስጊድ) በማንኛውም ማኅበረሰብ ላይ የሚያሳድረውን ሰፊና ጥልቅ ተፅዕኖ፣ በተለይም ደግሞ ታላቁ የኒውሃም መስጊድ ሊሠራ በታቀደበት ኅብረተሰብ መካከል የሚጭኑትን አጥፊ ውጤት በተመለከተ ለመናገር ብቃቱ ያላቸው ናቸው። ይህንን ዘገባ ማዘጋጀት ተገቢ እንዲያውም አስገዳጅ ሆኖ ስላገኙት ይህንን መስጊድን ለእስላማዊው ስልት ማዕከል እንደሆነ የሚያሳይና ከእስላማዊ ምንጮች በመነሳት በመስጊድ ውስጥ በተደረጉ ጊዜ ይቅርታን ስለሚያገኙ ተግባራት የሚያወሳ ጥልቅ ጥናት አዘጋጅተዋል። እስልምናን ሃይማኖት ከማለት ይልቅ “ስልት” ብለን ልንጠራው የመረጥነው ከመሐመድ ዘመን አንስቶ እስላማዊው ሸሪዓ ከፖለቲካ አንስቶ እስከ ምጣኔ-ሀብት ድረስ ሰው የሚመርጠውን ምርጫ በተመለከተ መልስ እንዳለው በጉልህ ስለሚወሳና፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሕይወት ያለ እስልምና ትርጉም-አልባ እንደሆነ ስለሚነገር ነው።

ደራሲዎቹ - ሙስሊም ምሁራን እንኳ እያንዳንዱን ስንክሳር ለማስተባበል እስከማይችሉ ድረስ - ከእስላማዊ ምንጮች የተገኙ፣ በአግባቡ በመረጃ የተደገፉ ማስረጃዎችን ብቻ ይጠቀሙ ዘንድ ተገቢውን ጥንቃቄ አድርገዋል። ነገር ግን እነዚህን ማስረጃዎች ጉዳዩን በቅን ልብ የሚመለከቱ ምዕራባውያን እና በዚህ አነስተኛ መጽሐፍ ውስጥ የተካተተውን ምልከታ ለመቀበል የማይፈልጉ ሌሎች ሰዎች ሊያጣጥሏቸው የሚችሉበት ሁኔታ አለ። ከሰላማዊና መቻቻልን የሚሰብኩ ማሳያዎቹ በተቃራኒ በዚህ ጥናት ውስጥ የሚገለጠውና በየዕለቱ በመስጊድ ውስጥ ተግባራዊ የሆነው እስልምና በየዜና አውታሮቹ ከምንሰማቸው አሸባሪዎች፣ አጥፍቶ ጠፊዎች፣ አል-ቃኢዳና የመሳሰሉት ጋር የሚመሳሰል ግብ እና አስተሳሰብ አለው። ይሁን እንጂ እነዚያው ሰዎች በመቻቻል፣ መጠንን በማወቅ፣ ማኅበራዊ እሴቶቻቸውን በመጠበቅ የሚታወቁት የእስላማዊው ኅብረተሰብ አካል የሆኑ ፅንፈኞች አይደሉምን?

አብዛኛዎቹ በአውሮፓ፣ ዋሽንግተን፣ ፓሪስ፣ በርሊን ወይም ሞስኮ የሚገኙ ልበ ቅን መሪዎቻችን ስለ ሰላማዊው የእስልምና ሃይማኖት ጥሩ ነገሮችን ተናግረዋል፣ እንዲሁም እጅግ ከሚያወድሷቸውና ሲያደንቋቸው ከምንሰማቸው ሙስሊም መሪዎች እና የንግድ ሰዎች ጋር ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊና ግላዊ ግንኙነትን መስርተዋል። እነዚህ ሙስሊም ሰዎችም በእርግጥም ቅን ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን እነርሱም እንኳን የራሳቸው የሃይማኖት ስልት ያለውን አጠቃላይ ምልከታ ያልተረዱ ይሆናሉ። ሆኖም፤ በጊዜ ብዛት እስልምና እንደገና ባንሰራራባቸው ያለፉ ክፍለ ዘመናት፣ ለምሳሌ በ1979 እንደተካሄደው የኢራን እስላማዊ አብዮት ያለ ቢከሰት እነዚህ ሰዎች ሊቋቋሙት በማይችሉት ሁኔታ ወደ ዋነኛው እስላማዊ የሃይማኖት ትምህርት መጎተታቸው አይቀርም።

በመሠረቱ በእነዚህ ለዘብተኛ ሙስሊሞች ልብ ውስጥ ቁጥሩ እየጨመረ በመጣ ሁኔታ እስላማዊ ተኃድሶ የማካሄድ ፍላጎት አለ። ልብ ብለን የተመለከትን እንደሆነም ዛሬም እንኳ በማደግ ላይ ያሉ የእስልምና ተሓድሶ እንቅስቃሴዎች፣ ዘመናዊነትን፣ ግላዊ ነፃነትን፣ የሃይማኖት ምርጫን፣ ጥብቅ እስላማዊ ሕግጋትን ማለዘብን እና የመሳሰለውን የሚሰብኩ እንቅስቃሴዎችን እንመለከታለን። እንዲህ ያለው ነገር በእርግጥም አስደሳች ይመስላል፤ ሆኖም ጥቂት የማሳሰቢያ ዓረፍተ ነገሮችን ልናሰፍር ይገባናል። እንዲህ ያሉት እንቅስቃሴዎች በእስልምና ታሪክ ውስጥ ሁሉ - መውደቅና መነሳትን - አሳይተዋል። ሁሉም የእስላማዊ ተሓድሶ ንቅናቄዎች በስተመጨረሻ ገሸሽ ተደርገው እንደ ጥቅም አልባ ነገር ተቆጥረዋል፣ ሽንፈት ገጥሟቸዋል ወይም ተወግደዋል። ለእንዲህ ያለው ውጤት ምንም እንኳ በመንግስት አወቃቀር ውስጥ በእስላማዊው የሸሪዓ ፍርድ ቤት በዳኝነት (ቃዲ) ቢያገለግልም በ3ኛው ክፍለ ዘመን በስፔን ኮርዶባ የእስልምና ተፈላሳፊ የነበረው የኢብን ሩሺድ  (በምዕራቡ ዓለም አቬሮስ በመባል ይታወቃል። በዕውቀት ቀመር ላይ በጥልቀት የጻፈ ሲሆን በአሪስቶትል ሥራዎች ላይ በመመሥረት በእስልምና እና በተፈጥሮ ሕግጋት መካከል እርቅን ማውረድን አስተዋውቋል። ስመ-ጥሩ የስነ-መለኮት አዋቂ ቶማስ አኩዊናስ ከፈላስፋው ጋር በተመሳሳይ ዘመን የኖረ ሲሆን የአቬሮስን ሥራዎች በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አዳዲስ ሐሳቦችን ለማስረጽ ተጠቅሞበታ) ትልልቅ ጥራዞች መቃጠላቸው ዓይነተኛ ምሳሌ ይሆነናል። እርሱ በአብዛኞቹ ሰዎች ዘንድ ይከበር የነበረና አሁንም ድረስ የሚከበር አሪስቶትል በአውሮፓና በእስላማዊው ዓለም እንዲታወቅ ጥልቅ ምርምር ያደረገ ተፈላሳፊ ቢሆንም  የጻፋቸው ጽሑፎች “እውነት” ከእስልምና ውጪም እንደሚገኝ አበክረው የሚያሳስቡ ስለ ነበሩ ሥራዎቹ “አምላክን እንደሚሳደቡ” ተደርገው ተቆጠሩ።

በዓለም ዙሪያ የሽብር ጥቃቶች እየተስፋፉ በሄዱ ቁጥር እነዚህ ምልከታዎች በምዕራቡ የዜና አውታሮች ድምጻቸው እየጎላና ዳግመኛ በመስጊድ እና ከመስጊድ የሚወጡ ፖለቲካዊና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን እየጠየቁ ነው።

ጉዳዩን ለዘብ ባለ ሁኔታ ለማስቀመጥ፣ የዛሬዋ ዓለም በእስልምና ስም ስለሚታዩ እንዲህ ያሉ ነገሮች ግራ ተጋብታለች። ግማሹ ሙስሊም ኅብረተሰብ በተለይ፤ በተለይ ሰብዓዊ መብትን፣ የምርጫ ነጻነትን እንዲሁም አል-ቃኢዳ ዋና ዋና እስላማዊ እሴቶችን ያንፀባርቅ እንደሆነ እያሰላሰሉ ግራ እንደተጋቡ አምናለሁ። በግሌ፣ አንዳች የተሓድሶ ተስፋ ስለ ነበረኝ ለአያሌ ዓመታት እስልምናን እንደ ከበረ ነገር ጠንቅቄ ስጠብቀው ነበረ። ባልታዛር እና አብድናጎ ሙስሊም በሆኑም ሆነ ባልሆኑ ሰዎች በአግባቡ ሊጤን የሚገባው ፈታኝ ሥራን አቅርበውልናል።

ምናልባትም ይህንን ዘገባ በቅጡ ካሰላሰላችሁ ተሓድሶ በክርስትና እና በአይሁዳዊነት ውስጥ እንደተሳካው በእስልምና ውስጥ መቼም እንደማይሳካ ለመገንዘብ ትችላላችሁ። እመኑኝ እንዲህ ማለቴ ተሳስቼ ቢሆን ኖሮ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን እውነታውን መጋፈጥ አለብን።

ጌዴዎን

አፕሪል፣ 2006

ወደ ማውጫው መመለሻ

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ