አጫጭር ዜናዎች 

ወደ አፍሪካ የእስልምና ጉዞ

አክራሪ የእስልምና ሃይሎች እየተንቀሳቀሱ ነው። አብዛኛዎቹ የጂሃድ ሰለባዎችም  በአፍሪካ ውስጥ ሲሆኑ እነዚህም የመጨረሻዎች አይሆኑም እያለ የአረብ የፖለቲካ ተንታኝና ጸሐፊ MICHAEL WIDLANSKI  በ16/02/2013 እንደሚከተለው ያቀርብልናል።

ሙስሊሞች «ሳቢል አላህ ፊ አል ሰይፍ» በማለት ብዙውን ጊዜ ይናገራሉ፤ ትርጔሜውም «የአላህ መንገድ በጔራዴ ነው» ማለት ነው። ይህም መንገድ በአንድ ወቅት ወደ ቪየና፣ ወይንም ስፔን፣ ወይን ፈረንሳይና ወይንም ሩቅ ምስራቅ መግቢያዎች የመራ  ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ አፍሪካ እያመለከተ ነው። 

የእስልምናን ዓላማና መርሆ እናራምዳለን በሚሉ ሃይሎች ማሊ፣ ሞሮኮ፣ አልጄሪያ፣ ሱዳን፣ ሊቢያ፣ ናይጄሪያና ግብፅ አሰቃቂ ሁኔታ እየደረሰባቸው ነው።

አለም ዝምብሎ ሲመለከት፣ እርምጃም ቢኖር በጣም የተጓተተ በመሆኑ የጦር መሳሪያዎች እየተበራከቱ ብዙዎች እየሞቱ ነው።

የተባበሩት የአለም መንግስታት ምን ማድረግ እንዳለበት ሲከራከር ልክ በሱዳን  በአስር ሺህ የሚቆጠሩ እንደታረዱ በመቶና በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ከማሊ እየጎረፉ ነው።

በአብዛኛው ዓመፅ የለሽ የነበረው የግብፅ ሰላማዊ አብዮት በሙስሊም ወንድማማቿች ተነጥቆ መሪያቸው አይሁዲዎችና ክርስቲያኖች ከዝንጀሮና ከአሳማ ነው የመጡት ይላል። የሲናን በረሃ ግብፅ እንደገና ወታደራዊ ቀጠና እያረገች ሲሆን አሜሪካም F-16 እና ተጨማሪ እርዳታን ልኳል።

በቱኒዝያ የገለልተኛ ተቃዋሚ መሪ ሲገደል፤ በግብፅና ናይጄሪያ ክርስቲያኖች ሲታረዱ  የእስልምና አጀንዳ በቱኒዝያና ግብፅ ከፍ እየተደረገ ነው። በአንድ ወቅት በእስልምና በሙሉና እንዲሁም በከፊል የተወረረ አካባቢ አሁን የእስልምና  ብቃት ይጎድለዋል በሚሉ እራሳቸውን «እውነተኛ ሙስሊሞች» ብለው በሚጠሩ  ሃይሎች እይታ ወድቆል።  መንደሮች በአልጅሪያና በናይጄሪያ ሲወድሙ ነዋሪዎቻቸው ብዙውን ጊዜ አንገታቸውን ይሰየፋሉ።

መሐመድ የተባለው ነቢይና የጦር መሪ  «የሰላም ሃይማኖት» ለሚለው በጂሃድ ስም መሬት እያካለለ ንጥቂያ ካደረገበት ጊዜ በኋላ አሁን እስልምና ሙስሊም ባልሆነው አለም ደጃፍ ላይ በሃይልና በከፍተኛ ድምፅ እያንኳኳ ነው።  በአንዳንድ ሁኔታ ጂሃድ ሰፊ ግዛትን ይዞ ለማረግገጥ የሚደረግ የበድዊን ጎሳ ግፊት የነበረ ሲሆን እርሱም በየጊዜው የሚደረጉ ወቅታዊ የዝርፊያ ወረራ ማለትም ጋዝዋ በመባልም ይታወቅ ነበር፡፡ ምሁራን እንደተገነዘቡት ጂሃድ ማለት የሃይማኖት ግዴታና ተግባራዊ ራስን መከላከያ ነበር።

ጂሃድ የእስላም «ስድስተኛው ምስሶ» ሲሆን አምስቱ ሌሎች መሰረታዊ ትእዛዞች “ካምሳት አርካን አል-እስላም” የሚባሉት ናቸው። ጂሃድ በሌላ አነጋገር ክርስቲያኖችና ይሁዲዎች የአስርቱ ትእዛዝ «አስራ አንደኛይቱ ትእዛዝ» እንደሚሉት ዓይነት ይሆናል ማለት ነው።

ይህ  ጠቃሚ መረጃ ቢሆንም በዋና ምዕራባዊያን ያሉት ባለስልጣኖች የፓለቲካዊ ትክክልነት አቋም ከመምረጣቸው የተነሳ እስልምና የሚያደርገውን የወረራ ጦርነት  በጥንቃቄ ተወት አድርገውታል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት በራክ ኦባማ ለመላው አገሪቱ ባደረጉት ንግግር  የእስልምና አሸባሪዎችን ፈረንሳይ ከማሊ ለማስወጣት  ለምታደርገው ጥረት ጥቂት የማመላለሻ አውሮፕላኖች በመስጠታቸው ራሱን አሞጋግሷል።

ኦባማ አልካይዳን አቅም አሳጥቻለሁ ቢልም የአልካይዳ ስራ የቀሰቀሳቸውና በአፍሪካ ከአልካይዳ ጋር ግንኙነት  ያላቸው ቡድኖች እርሱ በሚለው ላይ እያሾፉ ናቸው። ይህ ሁሉ ሲሆን አይናቸው በአፍሪካ ማእድን ላይ ያረፈው ቻይናና ሩስያ  የተለመደውን የዲፕሎማሳዊ ጨዋታ በመጠቀም «በአገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃገብነት» እንቃወማለን በማለት የእስልምናን ሽብርተኝነት በተዘዋዋሪ እየደገፉ ናቸው።

ኦባማና የሲአይኤ ተመራጭ ዳይሬክተር ጆን ብሬናን (John Brennan ) ለአንዳንድ የእስልምና እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ ወንድማማችነት በግብጽ  ልክ ጂሚ ካርተር (Jimmy Carter) አያቶላዎችን በኢራን አንዴ እንደደገፉ የተላሳለሰ አመለካከት በመያዝ ይባስ ብለው  እየደገፉ ነው። አረብኛ በቅጡ የማይናገረው ጆን ብሬንናን  በይፋ ጂሃድ «መንፈሳዊ ጉዞ» ነው በማለት ሲጠራው፤ ሁለቱም ማለትም ኦባማም ሆኑ እሱ እስልምና ወዴት እንደሚያመራ እናውቃለን ብለው ያምናሉ።

እስልምና የሚያመራው በአለም ከፍተኛ የእስልምና ተከታይ ቁጥር  ወዳላት ወደ ኢንዶኔዥያ ነው በማለት ያስባሉ፡፡
 
ኦባማና ጆን ብሬናን ሁለቱም ከፊሉን የወጣትነት ጊዜያቸውን በኢንዶኔዥያ አሳልፈዋል። እስላም ምን እንደሆነና ምን መሆን እንዳለበት ኢንዶኔዥያ ምሳሌ ነች ብለው ያምናሉ። ለብዙዎቹ ሙስሊሞች ሞዴላቸው ግን እነርሱ በወጣትነታቸው የሚያውቋት ኢንዶኔዥያን ሳትሆን ሜካን (Mecca) ናት፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን የምስራቅ እስያ እስልምናም ማለትም የኢንዶኔዥያ፣ የማሌዥያውና የፊሊፒንስ ከጊዜ ወደጊዜ በጣም አሸባሪና ፀረ-ምዕራባውያን እየሆነ መጥቷል።

አክራሪ የእስልምና ሃይሎች በፍጥነት ዘመቻ ላይ ናቸው። የምዕራባውያን ትብብር፣ የኦባማና የጆን ብሬናን ንግግር በፍፁም አይደንቃቸውም። አብዛኞዎቹ የጂሃድ ሰለባዎች አሁን የሚገኙት በአፍሪካ ነው፣  ይሁን እንጂ እነርሱ ምናልባትም የመጨረሻዎቹ ሰለባዎች ላይሆኑ ይችላሉ፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

የጽሑፉ አቅራቢ በአረብ ፖለቲካና ግንኙነት ላይ ኤክስፐርት ሲሆን በሕዝብ ደህንነት ሚኒስቴር ውስጥ የስልታዊ ጉዳዮች አማካሪ ነው፡፡ ከዚህም በላይ የሚከተሉትን መጽሐፍት Battle for Our Minds: Western Elites and the Terror Threat published by Threshold/Simon and Schuster. ጽፏል፡፡ ከላይ ያየነው የኤክስፐርቱ ጽሑፍ ምዕራባውያንና አንዳንድ አገሮች ስለአክራሪው እስልምና ዓለም አቀፍ ዘመቻ ምንም ግንዛቤ እንደሌላቸው በትክክል ያሳያል፡፡

እኛ እንደምናምነው ከሆነ የሁሉም እምነት ተከታዮች ሰብዓዊ መብታቸው ተጠብቆ ባሉበት አገራቸው ውስጥ በሰላም የመኖር ዕድል ሊያገኙ ይገባቸዋል፡፡ ይህ ለሰዎች ልጆች ሁሉ በፈጣሪ አምላክ የተሰጠ መብት በእስልምና አክራሪዎች በኩል ግን ምንም ትኩረት ያልተሰጠው ይመስላል፡፡ የእስልምና አክራሪዎች እንቅስቃሴ ከራሳቸው መጽሐፍ ትዕዛዝ ማለትም ከቁርአን ምዕራፍ 2.256 “በሃይማኖት ማስገደድ የለም” ከሚለው ውጭ የሆነ ነው፡፡

የዚህም ማስረጃው በሰሜን እና በሰሜን ምዕራብ አፍሪካ ውስጥ ገሃድ በወጣውና የብዙ ንፁሃን ሰዎች ደም መፍሰስ ነው፡፡ በማሊ፣ በሰሜን ናይጀሪያ፣ በቱኒዚያ በሞሮኮ በግብፅ እየሆኑ ያሉት ነገሮች ሁሉ አሰቃቂዎች ናቸው፡፡

እነዚህ ሁሉ ነገሮች የሚከተሉትን ጥያቄዎች ማለትም በእውነት እስልምና ለሰው ልጅ ጠቃሚ እምነት ከሆነ ስለምን ማስገደድ አስፈለገው? ስለምን በጦር መሳሪያ መስፋፋት አስፈለገው? ስለምን የሌላውን እምነት ተከታይና እምነቶቻቸውን አያከብርም? የሰው ልጅ አብሮና በሰላም መኖር አለበት ብለው ለሚያስቡ ሙስሊሞች አሁን የሚታየው ሁኔታ እምነታቸውን ቆም በማለት እንዲመረምሩት ሊያደርጋቸው ይገባል፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና ግን መልዕክቱም ስራውም በጣም የተለየ ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ለሚያስበው የሰው ልጅ ክቡር አምልኮ የሚያምነውን አስቦበት እንዲያምን የሚጠይቅ ነው፡፡ ሰዎች የእግዚአብሔርን የፍቅር የማዳን መልእክት ይሰማሉ፣ ሕይወታቸውንም ይመረምራሉ ከዚያም ከእግዚአብሔር የሚታረቁበትን እና እግዚአብሔር እራሱ ያዘጋጀውን መንገድ እንዲያስተውሉ ይነገራቸዋል፣ እራሳቸውም ያለማንም ማስገደድ ወይንም ማስፈራራት ከእውነተኛው እግዚአብሔር ምህረትን በመጠየቅ ንስሀ ገብተው እርሱ ባዘጋጀው አዳኝ በክርስቶስ ያምናሉ፡፡

ይህንን ያደረጉ ሰዎችም ውዲያውኑ ከእግዚአብሔር እጅ አዲስ ሕይወትን ይቀበላሉ፣ የመንግስተ ሰማይም ወራሾች ይሆናሉ፡፡ ይህ ሁሉ ምንም ግዴታ የሌለበት የፍቅር ጥሪ ነው፡፡ አንባቢ ሆይ ይህ ጥሪ ለእናንተም ነው፣ የመጽሐፍ ቅዱሱን እግዚአብሔርን ለማወቅ እና ከእርሱ ጋር አሁን ህብረት ለመመስረት የመንግስተ ሰማይም ወራሽ ለመሆን የሚጠቅማችሁን እውቀት የምታገኙበትን መጽሐፍ ቅዱስን እንድታነቡ እንጋብዛችኋለን፡፡ ጌታ ይባርካችሁ አሜን፡፡

የትርጉም ምንጭ: Islam's path to Africa

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ