ያልተለመዱ የቁርአን አባባሎች

M.J Fisher, M.Div.

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

በቁርአን ውስጥ እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ ያልተለመዱ አባባሎች ይገኛሉ፡፡ በመሐመድ ነቢይነት የማያምኑት (እስልምናን ያልተከተሉት) መሐመድን እንዲተቹት ያደረጓቸው ምክንያቶች እነዚህን ብዙ ተረቶች ሲያስታውሳቸውና ሲቀራቸው ሰምተው ነው፡፡ ተረቶችን እንደ እውነተኛ ታሪክ አድርጎ መደጋገሙ ልክ አለመሆኑን ጠቅሰው የማያምኑት መሐመድን እንደሚከሱት ቁርአን እራሱ በሚከተሉት ጥቅሶች ውስጥ ይናገራል 16.24፣ 25.5፣ 68.15፣ 83.13፡፡

እነዚህ ተረቶችን እንግዳ ያደረጋቸው ነገር ዛሬም እንኳን ቢሆን ሙስሊሞች ላልሆኑት ሁሉ በጣም ግልጥ ነው፡፡ በክፍሉ ውስጥ ‹የሪፕ ቫን ዊንክል› ተብሎ የሚታወቀው ዓይነት ተረት አለበት (‹አንቀላፍቶ መንቃት› ወይንም ‹ለረጅም ጊዜ አንቀላፍቶ ወይንም አዕምሮ ስቶ በድንገት አዲስ በሆነ ሁኔታ ውስጥ መንቃት› የሚባለው ዓይነት ተረት ነው)፡፡ ለምሳሌም ያህል አንዳንድ ወጣቶችን በእንቅልፍ ላይ ለ300 ዓመታት ያህል እንዲቆዩ ለማድረግ ፀሐይ አቅጣጫዋን መቀየሯ ይገኙበታል፡፡ ቁርአን ስለ አንድ ግዙፍ ሰው ይነግረናል፣ እሱም ወደ ምዕራብ አቅጣጫ በጣም ከተጓዘ በኋላ በቀኑ ማብቂያ ላይ ፀሐይ የምትጠልቅበትን ረግረግ ጭቃ ቦታ አይቶ እንደመሰከረ አቅርቦልናል፡፡ ሌላው ተረት ደግሞ በዝሆኖች ይጠቀም የነበረ የጦር ሰራዊት እንዴት በወፎች መንጋ እንደተሸነፈ የሚገልጠው ነው፡፡ ይህም የሆነው የወፎቹ መንጋ በዝሆኖቹ ጦር ሰራዊት ላይ የሸክላ ጠጠሮችን ያለማቋረጥ በመጣል ሙሉ ለሙሉ እንዳጠፏቸው ይናገራል፡፡ ሰንበትን የሻሩ አይሁዶች በአላህ አማካኝነት ወደ ጦጣነት እንዴት እንደተቀየሩ የሚነግረንም ተረት አለበት፡፡

በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እነዚያን ተረቶች የሚያሳዩት ስልሳ አራት ጥቅሶች ጠቅለል ተደርገው ቀርበዋል፡፡ በቁርአን ላይ ግን ረጃጅሞች በመሆናቸው አንባቢ ጥቅሶቹን እያገላበጠ ማንበብ ይኖርበታል፡፡

ቁርአን የሚከተሉትን ተረቶች ይናገራል

አንቀላፊዎቹ፡- በአንድ አምላክ በማመናቸው ምክንያት አንዳንድ ወጣቶችና ውሻቸው ሊቀጧቸው ከሚያሳድዷቸው ከጣዖት አምላኪዎች ሲሸሹ በአላህ ወደ አንድ ዋሻ ተመርተው ለብዙ ዓመታት ተኝተዋል፡፡ በዚህም ወቅት እነሱን ለመርዳት ፀሐይ የመዞሪያ መንገዷን ቀይራለች፡፡ በዚያም ምን ያህል ወጣቶች (ቁጥራቸውን) እንደበሩ ከአላህ በስተቀር ማንም አያውቅም ነገር ግን አንዳንዶች ሰባት ነበሩ ይላሉ፡፡ ከውሻቸውም ጋር ሲደመሩ ስምንት ይሆናሉ፡፡ ከአላህ በስተቀር ለምን ያህል ዘመን እንዳንቀላፉ ማንም አያውቅም አንዳንዶች ግን ለ309 ዓመታት ነው ይላሉ፡፡ 18.9-25፡፡

ከመቶ ዓመታት በኋላ ትንሳኤ፡- አንድ ተጠራጣሪ አንዲት የወደመችን ከተማ ተመልከቶ አላህ እንዴት የከተማዋን የጥንት ነዋሪዎች (በትንሳኤ) ሊያነሳቸው እንደሚችል ይደነቅ ይሆናል፡፡ አላህም ያንን ተጠራጣሪ ሰው እንዲሞት አድርጎት ከአንድ መቶ ዓመታት በኋላ እንዲነሳና ወደ ሕይወት እንዲመለስ አድርጎታል፡፡ እሱም ለምን ያህል ዓመታት ከዚህ ዓለም ላይ እንዳልነበረ ተጠይቆ የመለሰው መልስ ለአንድ ቀን ብቻ የሚል ነበር፡፡ ነገር ግን ለአንድ መቶ ዓመታት ተወስዶ እንደበረ ተነግሮታል፣ ከመቶ ዓመታት በኋላም ሲነቃ (ከሞት ሲነሳ) ሲሞት የተወውን ምግቡና መጠጡ አሁንም ትኩስ ነበሩ ነገር ግን አህያው ወደ ደረቅ ድንጋይነት ተቀይሮ ነበር፡፡ በእሱም ላይ የሆነው ነገር ለሰው ልጆች ሁሉ የመጨረሻው ትንሳኤ ምን እንደሚመስል ትልቅ ምልክት ነበር 2.259፡፡

እጅግ ልዩ የሆነው ሰው፡- ታላቅ የሆነና ሁሉን ነገር ለማድረግ እንዲችል ተደርጎ የተፈጠረ አንድ ሰው ነበር፡፡ ስሙም ዱዐል ቃርናይን ነበር፡፡ ካደረጋቸውም ሌሎች ነገሮች ባሻገር እስከ ሩቅ ምዕራብ ድረስ በጎዳና ተጉዞ ፀሐይ በጥቁር የረግረግ ጭቃ ውስጥ ስትጠልቅ ተመለከተ፡፡ እንደገናም በሌላ ጎዳና ወደ ሩቅ ምስራቅ ተጓዘና ፀሐይ ጉዞዋን ስትጀምር ለእሷ በጣም ቅርብ የሆኑ ዓይነት ሰዎችንም ተመለከተ፡፡ እነሱም ከፀሐይ ጨረር ቅርብነት የማቃጠል ኃይል ምንም ዓይነት በከላከያ ያልነበራቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ ሌላው የእሱ ስራም ደግሞ አንድ ትልቅ የሆነን ግድብ (ድልድይን) መስራት ነበር፡፡ ይህም ግድብ የተሰራው በሁለት እልም ያለ ገደል ባላቸው ተራራዎች መካከል ያለውን ቦታ ሙሉ ለሙሉ ሞልቶ ነበር፡፡ ግድቡም ተሰርቶ የነበረው በቀለጠ ነሐስ ተለብጦ ከነበረ ብረት ነው፡፡ እሱም እጅግ በጣም ትልቅ ስለነበር የጎግና ማጎግ ሕዝቦች ሊመዝኑት አልተቻላቸውም ወይንም ሊቆፍሩትና ጎረቤቶቻቸውን ለመረበሽ አልቻሉም ነበር፡፡ ይህም ታላቅ ግድብ እስከ ፍርድ ቀን ድረስ የሚኖር ነው 18.83-98፡፡

ዝሆኖችና ወፎች፡- ዝሆኖችን ተጠቅሞ የነበረ አንድ የጦር ሰራዊት አንድ ጊዜ በአላህ ተሸንፎ ነበር፡፡ የወፎች መንጎችን አላህ ልኮባቸው ከተጠበሰ ጭቃ (ሸክላ) በሆነ ድንጋይ አወረዱባቸው ከዚያም ቅጠሉ እንደተበላ አዝመራ ሁሉም ረገፉ 105.1-5::

የተለወጡ ጅኒዎች፡- አንዳንድ ጅኒዎች እስከ ሰማይ ጫፍ ድረስ ይበራሉ ይህም የቁርአን ንባብ የሚሰማበት ቦታ ላይ ለመገኘት በመፈለግ ነው፡፡ በአላህ ዙፋን አካባቢ የሚሆነውን እንዳይመለከቱ ለማራቅ የምትወረወርን ፍላፃ አዩ (ተወርዋሪ ኮከብ)፡፡ እነሱም የሰሙት መልእክት አላህ አንድ እንደሆነና ምንም ሚስት እንደሌለው ልጆችም እንደሌሉት የሚናገረውን መልእክት ነው መልእክቱንም አመኑ፡፡ እነሱም ሙስሊሞች ሆኑ፡፡ ስለዚህም አንዳንድ ጅኒዎች በእስልምና ያምናሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ የሲዖል እሳት ማቀጣጠያ ነዳጆች ናቸው 72.1-15፡፡

የአላህን ግመል መግደል፡- የታሞድ ሰዎች በነቢዩ በሳሌህ ማስጠንቀቂያን ተሰጥቷቸው ነበር ይህም ከጣዖታት አምልኮ እንዲመለሱ ነበረ ነገር ግን ከእርሱ ጋር ተከራከሩ፡፡ ሳሌህም ለታሞድ ሰዎች አላቸው፡- ‹አንዲት የአላህ ንብረት የነበረች የሴት ግመል ነበረች እሷም ምንም ጥቃት ሊደርስባት አያስፈልግም› ነገር ግን እነሱ ግመሏን ገደሏት፡፡ ሳሌህም ቀጥሎ እነሱ ከሦስት ቀናት በኋላ እንደሚቀጡ ትንቢትን ተናገረ፡፡ ትንቢቱን በተናገረበት ቀንም ጠዋት በፍንዳታ የተነሳ ሁሉም በቤቶቻቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ፡፡ እነሱ ሁሉም ሄደዋል 11.61-68፡፡

ሰንበትን የሻሩቱ ወደ ጦጣነት ተቀየሩ፡- አይሁዶች ማስታዎስ ያለባቸው ነገር አላህ ሰንበትን የሚሽሩትን አይሁዶች እጅግ አስጠሊ ወደሆነ ጦጣነት እንዴት እንደቀየራቸው ነው፡፡ ይህም ለሚመጣው ትውልድ ምልክት ይሆኑ ዘንድ ነው፡፡ 2.65፣66፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

በቁርአን ውስጥ ያሉት ተረት የሆኑ አባባሎች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ ሙስሊሞች እነዚህን ነገሮች እንዴት ነው የሚመለከቷቸው? በእርግጥ እንደዚህ ዓይነት ተረቶችን የእግዚአብሔር ቃል ይናገራልን? መሐመድ እነዚህን ተረቶች ሲናገር እና ከእግዚአብሔር የመጡ ናቸው ሲል በዘመኑ የነበሩ ሰዎች ተቃውመውታል፡፡ እነዚህ ከእግዚአብሔር አይደሉም ብለዋል ለዚህም ደግሞ በዚህ ጽሑፍ መግቢያ ላይ ያሉት የቁርአን ጥቅሶች ማስረጃዎች ናቸው፡፡ እኛስ እንዴት ነው ልናያቸው የሚገባን ምናልባት ሐሳባችንን እንደሚገባ ለመግለፅ ፍርሃት ወይንም ተፅዕኖ ይኖርብን ይሆንን? ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ይህ እንደዚህ በቀላሉ የሚታለፍ ነገር አይደለም የምንከተለውና የምናምነው ነገር በእውነት ላይ ያልተመሰረተ ከሆነ የዘላለም ሕይወት ተስፋ የሚባል ነገር ሊኖረን አይችልም፡፡ ማንም በተረት ላይ በተመሰረተ እምነት መንግስተ ሰማይ ሊገባ አይችልም፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ግን የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ለእንደዚህ ዓይነት ሰዋዊ የፈጠራ ተረቶች ጊዜና ቦታ የለውም፡፡ ምክንያቱም በመጀመሪያ መጽሐፍ ቅዱስ የመጣው ከእግዚአብሔር ነው የፈጠራ ተረት የለበትም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የሕይወትና የእምነት ነገር የምርና አሳሳቢ በመሆኑ ነው፡፡ ማለትም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተላልፈው የምርና እውነተኛ ለሕይወት የሚጠቅምን መልክት ነው፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች መሆናቸውንና የዘላለምም ፍርድ እንደሚጠብቃቸው በግልጥ ተቀምጧል፡፡ በዕብራውያን መልእክት ምዕራፍ 9.27 ‹ለሰዎች አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱም በኋላ ፍርድ ተመድቦባቸዋል› የሚልን ቃል እናነባለን፡፡ ስለዚህም - ከዚያ የዘላለም ፍርድ ኃጢአተኞች የሆኑ ሰዎች እንዴት ሊድኑ ይችላሉ? የሚለውን ጥያቄ መጠየቅ አግባብና ማስተዋል ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥቄ መልስ የሚሆን የምስራች መልእክት አለው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስም ወጥ መልእክት እንደሚከተለው ነው፡- ሰዎች በኃጢአታቸው ንስሐ እንዲገቡ፤ ይቅርታን እና ስርየትን ማግኘት እንዲችሉ ዋጋ በከፈለላቸው በጌታ በኢየሱስ ስራ እንዲታመኑ፤ በእርሱም በኩል ብቻ ወደ እግዚአብሔር እንዲመጡ ነው፡፡ ይህንን ያደረጉ ሰዎች ከዚህ በፊት በሕይወታቸው ያላዩትን አዲስ ሕይወትን፣ እውነተኛ ሰላምን፣ የኃጢአት ይቅርታን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላሉ፣ የዘላለምም ሕይወትን ወራሾች ይሆናሉ፡፡

አንባቢ ሆይ መጽሐፍ ቅዱስን ለራስህ አግኝና በልበ ሰፊነት አንብበው፣ የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ እርሱ እራሱ ይናገርሃል፡፡ ለውስጥ ሕይወት የሚናገር መጽሐፍ ነው፡፡ የእግዚብሔርን ፈቃድ እና ዕቅድ በግልፅ የሚናገር የእግዚአብሔር መጠቀሚያ ቃሉ ነው አግኝና አንብበው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ቃሉን በማንበብ የሚገኘውን ትልቅ በረከት እንዲሰጥህ ፀሎታችን ነው፡፡ እግዚአብሔር በምህረቱ ይርዳህ አሜን!

 

የትርጉም ምንጭ:Unusual Tales, Chapter 15 of "A Topical Study of the Qur'an From a Christian Perspective" by M.J Fisher, M.Div

ሙሉ መጽሐፉ በአማርኛ: ርእሳዊ የቁርአን ጥናት በክርስትና አይን ሲመረመር

 

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ